ሲውዲን በዊክሊክ መስራቹ ጁልያን አሳንጅ ላይ ተጀምሮ የነበረውን ክስ አቋረጠች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሲውዲን አቃቤ ህግ ዳይሬክተር በዊክሊክ መሰራች ጁልያን አሳንጅ ላይ የተጀመረው  የአሰገድዶ መድፈር ወንጀል ክስ እንዲቋረጥ መደረጉን አስታወቁ ፡

የ45 አመቱ አሳንጅ  ላይ የተከፈተው የክስ ዶሴ ከሰባት አመት በኋላ እንዲዘጋ መደረጉ ነው የተነገረው፡፡

መረጃ አፈትላኪው አሳንጅ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2012 ጀምሮ በለንደን የኢኳዶር ኤምባሲ ውስጥ በጥገኝነት እየኖረ ይገኛል፡፡

ሲውዲን የተጀመረው ክስ መቋረጡን ብትገልጽም ፥የብሪታኒያ ፖሊስ ግን ከወጣ በቁጥጥር ስር እንደሚያውለው እና ለአሜሪካ አሳልፎ እንደሚሰጠው ዝቷል፡፡

የለንደን ፖሊስ ለፍርድ ቤት እጅን አለመስጠት በሚል እስከ አንድ አመት የሚደርስ መጠነኛ ቅጣት እንደሚጥልበት ነው የገለጸው፡፡

ብሪታኒያ አሳንጅ አሜሪካ ተላልፎ እንዲሰጣት ጥያቄ ስለማቅረቧ ያለችው ነገር የለም፡፡

አሳንጌ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የአሜሪካን ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ሰነዶች እንዲያፈተልኩ በማድረጉ አሜሪካ በወንጀል እየፈለገችው ነው፡፡

የሲውዲን አቃቢ ህግ እንደሚለው ፥አሳንጅ በህጉ አንቀጽ መሰረት የተከሰሰበት የይርጋ ጊዜ እንደ አውሮፓ አቆጠጠር ከ2020 በፊት ሲውዲን ከገባ ክሱ እንደሚንቀሳቀስ ጠቁሟል፡፡

የአቃቤ ህጉ ዳይሬክተር ምርመራውን በለማካሄድ አለመቻላቸው እንደሚቆጫቸው ገልጸው፥ የጥፋተኝነት ብያኔም እንዳልተሰጠ ተናግረዋል፡፡

ዛሬ ዜናው ከተሰማ በኋላ ዊክሊኪ “ ከእንግዲህ ትኩረቱ ወደ ብሪታኒያ“ ዞሯል በሚል በቲዊተር ገጹ አስፍሯል፡፡

የለንደን ከተማ ፖሊስ ቀጣዩ እርምጃ ምን ሊሆን እንደሚችል ያለው ነገር የለም፡፡

ምንጭ፦ቢቢሲ

 

 

 

በእስክንድር ከበደ