የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ነሃሴ 5፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሳምሶን ወንድሙ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ከዚህ ቀደም የባለስልጣኑ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ የተለያዩ የስራ ሀላፊዎች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል።

በአጠቃላይም በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ በቁጥጥር የዋሉ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ ነጋዴዎች እና ደላሎች ቁጥር 55 ደርሷል።

በተጨማሪም በሙስና ተጠርጥረው ጉዳያቸው በህግ እየታዩ ካሉ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ ባለሀብቶችና ደላሎች ጋር ግንኙነት ያላቸው የ210 ግለሰቦችና ተቋማት ንብረት በፍርድ ቤት መታገዱ ይታወቃል።

እንዲሁም 15 የተጠርጣሪዎች እና ከተጠርጣሪዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው ኩባንያዎች ንብረትም ነው የታገደው።