በፀረ ተባይ መድሃኒት የተበከለ የእንቁላል ምርት በ15 አገራት ተሰራጭቷል

 

አዲስ አበባ ነሃሴ 5፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሆንክ ኮንግ እና ስዊዘርላንድ ጨምሮ በ15 የአውሮፓ እና ኤሲያ አገራት "ፊፕሮኒል" በተባለ ፀረ ተባይ የተመረዘ እንቁላል መሰራጨቱን የአውሮፓ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ይህንን ሁኔታ አስመልክቶ በሚቀጥለው በፈረንጆቹ መስከረም 26 ስብሰባውን እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

በፀረ ተባይ መድሃኒቱ የተመዘረዘ እንቁላል ጉዳይ በበልጅመና ጀርመን መካከል ሀይለኛ ጭቅጭቅ መነሳቱ ኮሚሽኑ አውስተዋል፡፡

በመሆኑም ስብሰባው ተካሂዶ መፍትሄ እስኪገኝ ድረስ በአገሮች መካከል ያለው እርስ በርስ የመወቃቀስ እና የመወነጃጀል ሁኔታ መቆም እንዳለበት ኮሚሽኑ ገልጿል።

ፊፕሮኒል የተባለ የፀረ ተባይ መድሃኒት ከእንስሳት ላይ ተባዮችን ለማጥፋት የሚውል ሲሆን፥ በአውሮፓ በጥቅም ላይ እንዳይውል የታገደ ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ