ባንግላዲሽ በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ የሮሂንጊያ ስደተኞችን ማይናማር እንድትረከባት ጠየቀች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ የሮሂነንጊያ ስደተኞችን አስጠልላ የምትገኘው ባንግላዲሽ ማይናማር እነዚህ ስደተኛ ዜጎቿን እንድትረከብ ጠየቀች።

በማይናማር ራኪን ግዛት የሚገኙ ሙስሊም የሮሂንጊያ ማህበረሰብ በአገራቸው የተፈፀመባቸውን መገለል እና ጥቃት ሸሽተው ወደ ባንግላዲሽ በመሰደድ ላይ ናቸው።

ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ ጀምሮ በዚህች የማይናማር ግዛት በተቀሰቀሰ ግጭት ምክንያት 370 ሺህ ሰዎች ወደ ባንግላዲሽ ተሰደዋል።

የባንግላዲሽ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሀሲና ባንግላዲሽ ዜጎቿን መልሳ እንድትቀበል የጠየቁት የሮሂንጊያ ስደተኞች የተጠለሉበትን ጣቢያ ከጎበኙ በኋላ ነው።

ማይናማር ጉዳዩን የያዘችበት መንገድ ዓለም አቀፍ ውግዘትን እያስከተለባት ነው።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ነገ በጉዳዩ ላይ ይመክራል።

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ