አፈ ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ ከምክር ቤቱ አፈ ጉባኤነት ለመነሳት ጥያቄ ማቅረባቸውን መንግስት አረጋገጠ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 28 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ ከምክር ቤቱ አፈ ጉባኤነት ለመነሳት ጥያቄ ማቅረባቸውን መንግስት አረጋገጠ።

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ አፈ ጉባኤው ጥያቄያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለድርጅታቸው ኦህዴድ አቅርበዋል።

የአፈጉባኤው ጥያቄ እየታየ መሆኑንም ነው ሃላፊ ሚኒስትሩ የነገሩን።

በተመሳሳይ አቶ አባዱላ ገመዳ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ፥ ከምክር ቤቱ አፈ ጉባኤነት ለመነሳት ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸው የሚለቁበትን ምክንያት ወደ ፊት አሳውቃለሁ ብለዋል።