ይርጋለም ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የአካባቢ ብክላ ተግባሩን ካልተስተካከለ እንደማይከፈት ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ የአደይ አበባ የአሁኑ ይርጋለም ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የአካባቢ ብክላ ተግባሩ ካልተስተካከለ አይከፈትም ሲል የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀጋዬ ገብረማርያም ለፋና ብሮድካስቲግ ኮፖሬት እንደተናገሩት፥ ፋብሪካው በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውም ማስተካከያ ባለማድረጉ ምክንያት ከሰባት ቀን በፊት ፋብሪካው እንዲዘጋ ተደርጓል።

ፋብሪካው በአካባቢው ያደረሰው የብክለት መጠን በላብራቶሪ ተፈትሾ ከደረጃ በላይ በመሆኑ ነው እንዲዘጋ የተደረገው ተብለዋል።

እንደ አቶ ፀጋዬ ገለጻ ፋብሪካው በቀጣይም የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት ካላሰተካከለ ፋብሪካው እንደማይከፈት ነው የገለፁት።

ባለስልጣኑ በዚህ መልኩ የጀመረውን የእርምጃ ስርዓት በማስቀጠል በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ስድስት የቆዳ ፋብሪካዎች ላይም ተመሳሳይ የመዝጋት እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ለዚህም ለፋብሪካዎቹ አካባቢን በመበከላቸው እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ማረጋገጫ መስጠቱን ነው ሃላፊው የተናገሩት።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

በታሪክ አዱኛ