በሶሪያ አታሬብ ገበያ በተፈፀመ የአየር ድብደባ የ53 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰሜናዊ ሶሪያ በአሸባሪዎች ቁጥጥር ስር በምትገኝ ከተማ ውስጥ በተፈፀመ የአየር ድብደባ ቢያንስ 53 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ።

በማኅበራዊ ትስስር ድረ ገፆች ላይ በስፋት የተሰራጨው ቪዲዮ አንደሚያሳየው ጥቃቱ በአታሬብ ገበያ የደረሰ መሆኑን እና ከፍተኛ ዱዳት መድረሱን ያሳያል።

የአይን እማኞች እንደተናገሩት የጦር አውሮፕላኖች በገበያው ሶስት ጊዜ ድብደባ አካሂዷል።

ድብደባው ያደረሱት የጦር አውሮፕላኖች ከየት ወገን እንደመጡ እስከአሁን ግልፅ የሆነ መረጃ የለም ነው የተባለው።

ከተማዋ የምትገኘችው በሩሲያ እና በኢራን በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጀመርያ ላይ የተመሰረተው ነፃ ቀጠና ክፍል በሆነው በአሌፖ ግዛት ውስጥ ነው።

እነዚህ ዞኖች በቀጠናው የሚታዩ ጥቃቶችን ለመቀነስ ተብለው የተፈጠሩ ቢሆኑም፥ ይሁን እንጂ የማያቋርጥ ግጭቶች እየተካሄዱባቸው እንዳሉ ተገልጿል።

አካባቢው በአብዛኛው በተቃዋሚ ኃይሎች እና ከአልቃኢዳ ጋር የተቆራኙ አንድ የጂሃዲስቶች ቡድን የተያዘ መሆኑንም ተጠቁሟል።

መቀመጫው በኢንግሊዝ ያደረገው የሰብአዊ መብት ታዛቢ ተቋም እንደገለፀው፥ በአየር ድብደባው ከተገደሉት ውስጥ ህፃናት ይገኙበታል።

ታዛቢ ተቋሙ እና የሶርያ የስቪል መከላከያ፥ የሟቾቹ ቁጥር 53 መድረሱን ተናግረዋል።

በጥቃቱ ከ100 በላይ ሱቆች የያዘው ጠቅላላ ገበያ መደምሰሱንም ተገልጿል።

_1.jpg

አታሬብ ከአውሮፓውያኑ 2011 ጀምሮ በሶርያ በደረሰው ግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሶሪያውያን መኖሪያ መሆኗ ይነገርላታል።

በሶሪያ በተከሰተው የእርስ በእርስ ግጭትም እስከአሁን ድረስ ቢያንስ 400 ሺህ ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።

ምንጭ፥ ቢቢሲ