የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቋንቋ ማበልፀጊያ ማዕከል ማቋቋሙን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቋንቋ ማበልፀጊያ ማዕከል ማቋቋሙን አስታወቀ።

የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አፀደወይን እንደተናገሩት፥ ለተማሪዎች ውጤት ዝቅ ማለት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ውሰንነት ይጠቀሳል።

ይህን ችግር ለመቅረፍም ዩኒቨርሲቲው የቋንቋ ማበልፀጊያ ማዕከል በማቋቋም ወደ ስራ መግባቱን ገልፀዋል።

ከዚህም ባሻገር ለመምህራን የሚሰጠውን የእውቀት ማሻሻያ ስልጠና በማጠናከር ጥራት ያለው የትምህርት ስርአት እንዲጎለብት እየሰራን ነው ብለዋል።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 5ኛውን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥራት ጉባኤ ከባለፈው አርብ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ማስተናገዱም ይታወሳል።

በሙሉጌታ ደሴ