ትራምፕ ጦራቸውን ከሶሪያ እንዳያስወጡ አሳምኛቸዋለሁ - ማክሮን

አዲስአበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2010 (ኤፍቢሲ) የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጦራቻውን ከሶሪያ በቶሎ እንያስወጡ ማሳመናቸውን አስታወቁ።

ማክሮን በቴሌቪዥን ላይ በነበራቸው ቃለ መጠይቅ ትራምፕ ከ10 ቀናት በፊት ጦራቸውን ከሶሪያ ምድር ስወጣት እንደሚልጉ ማስታወቃቸውን አንስተው፥ አሁን ግን ለረዥም ጊዜ በሶሪያ እንዲቆዩ እንዳግቧቧቸው ነው የጠቀሱት።

ከዚህ ቀደም ትራምፕ ጦራቸውን ከሶሪያ በቶሎ እንደሚያስወጡ ይፋ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።

የማክሮን ንግግር ከተሰማ በኋላ የዋይት ሃውስ ቃለ አቀባይ የሆኑት ሳራ ሳንደርስ የአሜሪካ ተልዕኮ እንዳልተለወጠ ጠቅሰው፥ አሁንም ቢሆን ፕሬዚዳንቱ በተቻለው ፍጥነት ጦሩ ከሶሪያ እንዲወጣ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

ትራምፕ ባለፈው ሳምንት በሶሪያ ላይ ጥቃት እንደሚሰነዝሩ ይፋ ባደረጉበት ወቅት አሜሪካ በሶሪያ መቆየት እንደማትፈልግ በድጋሚ አስታውቀዋል።

ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ እና አሜሪካ የፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድ አስተዳደር የኬሚካል ጦር መሳሪያ ተጠቅሟል በሚል በጋራ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ጥቃት የሰነዘሩ ሲሆን የተሳካ እንደነበርም ገልጸዋል።

አሜሪካ በምስራቃዊ ሶሪያ ኩርዶችንና የአረብ ሚሊሻ በመባል የሚጠሩትን የሚደግፉ 2 ሺህ ዜጎች አሰማርታለች።

 

 


ምንጭ፦ ቢቢሲ
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ