የቻይናው ፕሬዚዳንት ማስጠንቀቂያ ለታይዋንና አሜሪካ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2010 (ኤፍቢሲ) የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂን ፒንግ በአካባቢው የጦር ልምምድ እንዲደረግ በማዘዝ በታይዋንና አሜሪካ መካከል ላለው ግንኙነት ማስጠንቀቂያቸውን አስተላልፈዋል።

በሁለቱ ወገኖኝ ግንኙነት ደስተኛ ያልሆነችው ቻይና በታይዋን ሰርጥ ላይ የቤጂንግ የባህር ሀይል እውነተኛ ጥይትን በጥቅም ላይ በማዋል ወታደራዊ ልምምድ እንዲደረግ አዛለች።

ይህም በመሆኑ ረቡዕ የሚካሄደው ወታደራዊ ልምምድ በዓይነቱ የመጀመሪያ ነው ተብሏል።

ቻይና ግዛቴ ናት የምትላት ታይዋን በ2015 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማካሄዷ የሚታወስ ነው።

ከዚህ ቀደም ፕሬዚዳንት ሺ ለመጀመሪያ ጊዜ ከታይዋን የቀድሞ ፕሬዚዳንት ማ ነግ ጂኦ ጋር ከተወያዩ በኋላ ግንኙነታቸው የተሻሻለ ቢሆንም፥ በሀገሪቱ በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዛ ኢንግ ዌን መምጣታቸውን ተከትሎ ግንኙነታቸው ሻክራል።

 

 


ምንጭ፦ ሲኤንኤን
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ