ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ከግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሾኽሪያ እና ከደህንነት ዳይሬክተሩ አባስ ከማል ጋር ተገናኝተው ተወያዩ፡፡

ውይይቱን ያካሄዱት አዲስ አበባ ሲሆን፥ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ከሀገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሦስትዮሽ ስብሰባ ጎንለጎን ነው ተብሏል፡፡

ዶክተር አብይ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት እንደሚያጠናክሩ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፕሬዚዳንት አብድልፈታህ ኤልሲሲ ለዶክተር አብይ አህመድ ግብጽን እንዲጎበኙ ግብዣ እንዳቀረቡላቸውም አስታውቀዋል፡፡