አሜሪካ የትራምና የኪም ውይይት በታቀደለት መሰረት እንደሚካሄድ ተስፋዋን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩናይትድ ስቴትስ ከሰሜን ኮሪያ የተሰነዘረው ማስጠንቀቂ እንዳለ ቢሆንም፤ በሰኔ የሚካሄደው ውይይት በታቀደ ጊዜ እንደሚካሄድ ተስፋዋን ገች፡፡

የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ሳራ ሳንደርስ ዶናልድ ትራምፕ ለውይይቱ አሁንም ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን ውይይቱ በታቀደለት ጊዜ የማይካሄድ ከሆነ ሀገራቸው በሰሜን ኮሪያ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጫና ወደ መፍጠር እንደምትሄድ አስታውቀዋል፡፡

ሰሜን ኮሪያን ክፉኛ አስቆጥተዋል ከተባሉት ግለሰቦች መካከል የዩናይትድ ስቴትስ የደህንነት አማካሪ ጆን ቦልተን ይገኙበታል፡፡

ጆን ቦልተን በቴሌቪዥን ቃለመጠይቅ ወቅት ሰሜን ኮሪያ ከኒውክሌር ነጻ ለመሆን የሊቢያ ዓይነት ሞዴል መከተል አለባት ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ይህንን ተከትሎ ታዲያ የኮሌኔል ጋዳፊን መጨረሻ ለተመለከቱት ኪም የቦልተን አስተያየት ሊዋጥላቸው አልቻለም ነው የተባለው፡፡

በሌላ በኩል ከደቡብ ኮሪያ ጋር ዛሬ ሊያካሂዱት የነበረውን ውይይት በዩናይትድ ስቴትስና በደቡብ ኮሪያ ዓመታዊ ወታደራዊ ልምምድ ምክንያት መሰረዟን ጧት ማስታወቋ ይታወቃል፡፡

ትራምፕና ኪም ሲንጋፖር ላይ ሰኔ አምስት የጋራ ውይይት ለማካሄድ ቀጠሮ መያዛቸው የሚታወስ ነው፡፡

 

 


ምንጭ፦ቢቢሲ
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ