የአፍጋኒስታን ወቅታዊ ጉዳይ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት የቀጣይ ትኩረት ነጥብ ሆኗል

አዲሰ አበባ፣ ሃምሌ 05፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአፍጋኒስታን ወቅታዊ ጉዳይ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት የቀጣይ ትኩረት ነጥብ እንደሆነ ተገለጿል።

በሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት መሪዎች የ2ኛው ቀን ስብሰባ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግፊት ድርጀቱ በአፍጋኒስታን ግጭት ላይ ትኩረት ሰጥቶ ለመስራት ዕቅድ መያዙ ነው የተገለጸው። 

 አባል ሀገራቱ ከአሁን በፊትም በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር ለዚሁ ጉዳይ ወጭ እያደረጉ ቢሆንም በቂ ያለመሆኑንና ተጨማሪ ዶላር መበጀት አስፈላጊ መሆኑን ፕሬዚዳት ትራምፕ ተናግረዋል።

በዚህም አባል ሀገራቱን ከዓመታዊ ገቢያቸው 4 በመቶ ያህሉን ለድርጅቱ ወታደራዊ ወጪ መመዳብ አንዳለባቸው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ጠይቀዋል ተብሏል።

የአፍጋኒስታኑ ፕሬዚዳነት አሽራፍ ግሃኒ ከሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት መሪዎች ጋር ይገናኛሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፥ እስከ ፈረንጆቹ 2024 የሚቆይ የጸጥታ ሃይል ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚችልም ተመላክቷል።

አሁን ላይም የብሪታኒያዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይ ለዘርፉ ድጋፍ የሚያደርጉ 440 የጦር ሰራዊት አባላት ለመላክ መወሰናቸውም ታውቋል።

አሜሪካበ በኩሏ 3ሺህ ወታደሮቿን ለመላክ የወሰነች ሲሆን፥ በ2017 ለተመሳሳይ ተግባር በአፍጋኒስታን ካሰማራቻቸው ወታደሮች ጋር በአጠቃላይ 15 ሺህ ወታደሮችን ድጋፍ ማድረጓን ዘገባው አስታውሷል።

 

ምንጭ፦ bbc.com

የተተረጎመውና የተጫነው፦ በእንቻለው ታደሰ