የህብረቱን 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ጉብኝት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጭው ግንቦት ወር የሚከበረውን የአፍሪካ ህብረት 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ጉብኝት ተካሄደ ።

በጉብኝቱ የህብረቱ የምስረታ በዓል ኮሚቴ አባላት ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ጋዜጠኞች ተሳትፈዋል።

በ705 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈውና ከ240 በላይ የእጽዋት ዝርያዎች የሚገኙበት የጉለሌ እጽዋት ማእከል በቅድሚያ ተጎብኝቷል።

በማዕከሉ በ2 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ የአፍሪካ ካርታ ምስል የሚዘጋጅ ሲሆን ፥ ከ55ቱም የአፍሪካ ሀገራተ የተውጣጡ ተወካዮችም በስፍራው የመታሰቢያ ችግኝ ይተክላሉ ነው የተባለው ።

በመቀጠል ከአፍሪካ ህብረት- ቄራ - መስቀል አደባባይ - ቦሌ የሚደርሰው የ 5.9 ኪሎ ሜትር መንገድ ተጎብኝቷል።

ለህብረቱ 50ኛ አመት የምስረታ በዓል ግንባታው በመፋጠምን ላይ የሚገኘው ይህ የመንገድ ፕሮጀክት በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ ቢሆንም ፥ 30 ሜትር የሚረዝመውን ድልድይ ጨምሮ ከህብረቱ አዳራሸ እስከ ቄራ ያለው መንገድ ግንባታ ላይ ግን መጓተት እየተስተዋለበት እንደሚገኝ ነው በጉብኝቱ ወቅት የተመለከተው።


በባሃሩ ይድነቃቸው

Comments

Name *
Submit Comment