Fana: At a Speed of Life!

ሀረር የጤና ሳይንስ ኮሌጅ 969 የጤና ባለሙያዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 10፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ሀረር የጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በዲግሪና ዲፕሎማ ያሰለጠናቸውን 969 የጤና ባለሙያዎችን በዛሬው እለት አስመርቋል።

ኮሌጁ ዛሬ ለ25ኛ ጊዜ ያስመረቃቸው ምሩቃን 508 በዲግሪ ሲሆን 461 በዲፕሎማ ነው።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ እንደተናገሩት ሀገራዊ ብልፅግናን ከማረጋገጥ አንፃር የጤናውን ዘርፍ ማጎልበት ወሳኝ ነው።

በተለይም ተላላፊ በሽታንና በወሊድ ሳቢያ የሚከሰቱ ሞትና ህመምን ለመቀነስ በቂና ብቁ የጤና ባለሙያዎችን ማፍራት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

የሀረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን አቶ ያሲን አብዱላሂ በበኩላቸው ኮሌጁ ከትምህርት ስልጠና በተጨማሪ የጤና ሙያ ማሻሻያ ስልጠናና ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በመስራት ጠንካራ መሰረት በማኖር ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ከዚህ ባለፈም ኢኮኖሚያዊ አቅማቸው ውስን ለሆኑ 398 ተማሪዎች የነፃ ትምህርት እንዲያገኙ እገዛ ማድረጉንም አመላክተዋል።

በተላይም  ዘንድሮ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የተቀመጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ እንዲያጠናቅቁ ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል።

በእለቱም የተመረቁት እጩ የጤና ባለሙያዎችም 220 በተከታታይ እና 288 በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም እንዲሁም 461 በደረጃ አራት ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ዘርፍ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በተሾመ ኃይሉ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.