Fana: At a Speed of Life!

ሀሰተኛ መታወቂያ ሲያትሙ የነበሩ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀሰተኛ የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት መታወቂያ ሲያትሙ የነበሩ ግለሰቦች እጅ ከፍንጅ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

ሀሰተኛ የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት መታወቂያ የሚያባዙና መታወቂያውን የሚያሰሩ ሰባት ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት ፒያሳ “ሮቤል የጽህፈት መሳሪያ መሸጫ” ተብሎ በሚጠራው ድርጅት ውስጥ ሀሰተኛ መታወቂያ እያተሙ በነበረበት ወቅት መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ግለሰቦቹ አንድ ሀሰተኛ መታወቂያ ለማተም÷ 10 ሺህ ብር እየተቀበሉ እንደሚሰሩም ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሀሰተኛ መታወቂያዎቹ ወንጀል ሊፈጸምባቸው የሚችሉ እንደሆነም ፖሊሲ በመረጃው አመላክቷል፡፡

ከተጠርጣሪዎች ጋር በኤግዚቢትነት በፍትሕ ሚኒስቴር፣ በኢትየጵያ ንግድ ባንክ አራዳ ጊዮርጊስ ቅርንጫፍ፣ በደቡብ ክልል ሀድያ ዞን ፍትሕና ጸጥታ ቢሮ እንዲሁም በፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫ ምዝገባ ኤጀንሲ እና ሌሎች ተቋማት ስም የተዘጋጁ ሀሰተኛ ማህተሞች ተይዘዋል፡፡

ሀሰተኛ መታወቂያ ሲያባዙ የተያዙት ግለሰቦች በህብረተሰቡ ጥቆማ የተያዙ ሲሆን አሁንም የመዲናዋ ነዋሪዎች ሀሰተኛ ሰነድ የሚሰሩ ሰዎችን መረጃ ለፖሊስ በመስጠት ወንጀለኞችን በማጋለጥ የሚያደርጉት ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠይቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.