Fana: At a Speed of Life!

ሀብታችንን በሚገባ በመጠቀም የህዝቡን ፍላጎት ለማሟላት እንሠራለን – የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳዳር

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲሱ የክልሉ ምክር ቤት የተመረጡት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ቀጣይ የክልሉን ህዝብ ፍላጎት ለማሟላትና ለጥያቄያቸው ምላሽ ለመስጠት የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የራስን አንድነት ከማጠናከር ባለፈ ከሀገሪቱ ህዝቦች ጋር ያለንን ወንድማማችነት አጎልብቶ መቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ችግሮችን በንግግር የመፍታትና ዲሞክራሲያዊ አካሄድን መከተል አስፈላጊ መሆኑን የገለፁት አቶ ደስታ ሌዳሞ በኪራይ ሰብሳቢነት ላይ የሚደረገው ትግል መጠናከር እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
ሰፊ የስራ እድል ፍላጎት ያለ በመሆኑ በኢንዱስትሪና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
በክልሉ የሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮችም ለስራ እድል ፈጠራ ስራዎች ላቅ ያለ ፋይዳ እንዳላቸው ጠቁመው÷ የበለጠ መሥራት እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡
በግብርናው ዘርፍ ከፍ ያለ ተግባራትን ማከናወን እንደሚገባ ገልፀው ያለውን ሀብት በአግባቡ መጠቀም ይገባል ብለዋል፡፡
በግብርናው ዘርፍ ተዝቆ የማያልቅ ሀብት ያለ በመሆኑ በትኩረት መስራት እንደሚገባማ አስገንዝበዋል፡፡
በብርሃኑ በጋሻው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.