Fana: At a Speed of Life!

ሀዲያ ሆሳዕና ጅማ አባ ጅፋርን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ12ኛው ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀዲያ ሆሳዕና ጅማ አባ ጅፋርን 1 ለ 0 አሸነፈ፡፡

የሀዲያ ሆሳዕናን የማሸነፊያ ብቸኛ ግብ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ካሉሻ አልሃሰን አስቆጥሯል፡፡

የሊጉ መሪ ፋሲል ከነማና ሰበታ ከተማ ጨዋታቸውን ከሰዓት በባህርዳር ስታዲየም ያካሄዳሉ፡፡

ሊጉን ፋሲል ከነማ በ28 ነጥብ ሲመራ ኢትዮጵያ ቡናና ቅዱስ ጊዮርጊስ እኩል 24 ነጥብ ይዘው በግብ ክፍያ በመበላለጥ ሁለተኛ እና ሦስተኛ በመሆን ይከተላሉ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.