Fana: At a Speed of Life!

ሀገራቱ የኑክሌር የጦር መሳሪያ ውድድር ላለማድረግ ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምስቱ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ የታጠቁ ሀገራት ከሚያደርጓቸው የኒውክሌር የጦር መሣሪያ ውድድሮች እንደሚታቀቡ በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

ቻይና ፣ ሩሲያ፣ ፈረንሳይ፣ ብሪታንያ እና አሜሪካ የጸጥታው ምክር ቤት አባላት ሲሆኑ፥ የኒውክሌር ጦርነት ለማስቀረት ለተደረገው ስምምነት ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል፡፡

አባል አገራቱ በኑክሌር ጦርነት ማሸነፍ እንደሌለ በመገንዘብ የኑክሌር የጦር መሳሪያ ላለማስፋፋት እና ውድድር ላለማድረግ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን በመግለጫቸው አረጋግጠዋል ነው የተባለው።

ሀገራቱ በመግለጫቸው እንዳስታወቁት በሀገራት መካከል አለመግባባት ሲፈጠር ችግሮችን በጠረጴዛ ዙርያ በውይይት መፍታት እንጂ በጦርነት እንደማይፈታ መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡

ግንኙነታቸው በመከባበር እና በመደጋገፍ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን፣ ግጭቶች ሲፈጠሩም በውይይት ለመፍታት መስማማታቸውን አገራቱ በጋራ መግለጫቸው አስታውቀዋል።

አምስቱ ሀገራት ያልተፈቀደ የኑክሌር ጦር መሳሪያን ለመከላከል የሚወስዱትን እርምጃ አጠናክሮ ለመቀጠል ያላቸውን ፍላጎትም አሳይተዋል።

የኑክሌር የጦር መሳሪያዎች ራስን ለመከላከል ዓላማ ብቻ ማዋል እንዳለባቸውም አስምረውበታል ሲል ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.