Fana: At a Speed of Life!

ሀገራዊ ምክክሩን ውጤታማ ለማድረግ ያለመ የምሁራን ውይይት በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ብሄራዊ ምክክሩን ከማሳካት አንጻር የምሁራን ሚና” በሚል መሪቃል ሀገራዊ ምክክሩን ውጤታማ ለማድረግ ያለመ የምሁራን ውይይት በአሶሳ ዩኒቨርስቲ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሄራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር÷ ሀገራችን “እንቆቅልሽ በሚመስል መልኩ ለገጠማት ችግር መፍትሄው ውይይት ብቻ ነው” ብለዋል።
ለዚህም ሀገራዊ ምክክሩ መፍትሄ አንደሚሰጥ ይጠበቃል÷ ምሁራንም ሚናቸውን እየተወጡ ስለመሆኑ ራሳቸውን መጠየቅ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ከማል አብዱራሂም ÷ የውይይት መድረኩ ዓላማ በሀገራዊ ጉዳዮች የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት አስተዋጽኦ ለማበርከት ነው ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲው ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ተፈናቃዮችን ከመደገፍ ጀምሮ ለሰላም መጠናክር የድርሻውን እያበረከተ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.