Fana: At a Speed of Life!

ሀገራዊ የስፓሽያል የልማት ማዕቀፍ አውደጥናት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የከተማ ልማት ሥራ ክፍል ጋር በመተባበር ሀገራዊ የስፓሽያል የልማት ማዕቀፍ አውደጥናት ተጀመረ፡፡
በአውደጥናቱ የየክልሎች የፕላንና ልማት ተቋማት፣ የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ፣ የግብርና እና የአርብቶ አደሮች እንዲሁም ከከተማ እና ኮንስትራክሽን ቢሮዎች የተውጣጡ የዘርፉ ባለሞያዎች መሳተፋቸው ተገልጿል፡፡
ለሦስት ቀናት የሚቆየውን አውደጥናት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እና አማካሪ አቶ ገረመው ነጋሳ ያስጀመሩት ሲሆን÷ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የነበራትን የኢኮኖሚ ዕድገት አንስተዋል፡፡
በኢትዮጵያ ዘላቂ እና ሁሉን አካታች ልማት ለማምጣት ለተለያዩ የሀገሪቱ ችግሮች መፍቻ ሊሆን የሚችለውን የስፓሽያል ልማት ማዘጋጀት በጣም አስፈላጊና ወቅታዊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

 

በተመረጡ የልማት ኮሪደሮች የኢንደስትሪ ፓርኮችን እና የክልል ከተሞችን ኢንዱስትሪ ለማሳደግ፣ ሆርቲካልቸር እና የቱሪዝም ማዕከላት የልማት እቅዶች በዕቅድ ውስጥ ተካተው ተግባራዊ እንደተደረጉ ጠቅሰዋል፡፡
የከተማ ስፓሽያል ፕላን፣ የትራንስፖርት ማስተር ፕላን እና ሌሎች ማዕቀፎች እንዳሉ የተገለጸ ሲሆን÷ በሀገሪቱ ስፓሽያል ፕላንን በሚመለከት ግልፅ የሆነ ራዕይ፣ አላማ እና ስትራተጂ በማዘጋጀት እስካሁን ተግባራዊ አልተደረገም ተብሏል፡፡
በተበጣጠሰ መልክ ሲከናወን የነበረውን የስፓሽያል ልማት እና ፕላን በተደራጀ መልክ ሀገራዊ የልማት ግቦችን ባማከለ መልኩ እንዲከናወን ለማድረግ የሚያስችል ማዕቀፍ እንደሚሆን አቶ ገረመው አመልክተዋል፡፡
ሀገራዊ የስፓሽያል ልማት ማዕቀፉ ሲጠናቀቅ÷ በሀገሪቱ ውስጥ የልማት ማዕከሎችን፣ የልማት ቀጠናዎችን፣ የኢኮኖሚ ዞኖችን በመለየትና በልማት ወደ ኋላ የቀሩ ቦታዎችን የሚደግፍ የልማት ፕሮግራም በማዘጋጀት የአስር ዓመቱን የብልፅግና እቅድ ለማሳካት እንደሚረዳ እንዲሁም ዘላቂ ልማትን የሚያረጋግጥ እንደሆነ መግለጻቸውን ከፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.