Fana: At a Speed of Life!

ሀገሬ በምትፈልገኝ አገልግሎት እሰማራለሁ-ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በቀጣይ ሀገሬ በምትፈልገኝ አገልግሎት እሰማራለሁ ሲሉ ገለጹ፡፡
ለኢንጂነር አይሻ መሀመድ የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ሚንስትር እና ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ሁለቱም ዘርፎች ለአገራችን ማደግና መለወጥ ወሳኝ ተቋማት ናቸው ያሉት ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ÷ በውጤታማነት እንደምትመሩት ባለሙሉ እምነት ነኝ፤ ድጋፌም አይለያችሁም ሲሉ አረጋግጠዋል፡፡
ውድ የሃገሬ ህዝቦች÷ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ላለፉት 5 አመታት ሚኒስትር በመሆን አገልግያለሁ፤ አስቸጋሪ ጊዜያትንም አሳልፈናል ብለዋል፡፡
ግድባችንም በጥቂት ወራት ሀይል እንደሚመነጭ ጠቁመው÷ በዚህና በሌሎችም መስኮች ያደረግሁት አስተዋጽኦ በፈታኞቹ ወቅቶችና ሰአታት አገሬን ቀና አድርጓታል ብዬ አምናለሁም ብለዋል፡፡
በቀጣይ ሃገሬ በምትፈልገኝ አገልግሎት የምሰማራ ይሆናል፤ ለነበረኝ ትልቅ ኃላፊነትና ለተደረገልኝ ትብብር አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡
አገራችን ኢትዮጵያን ፈጣሪ ይጠብቃት፤ ኢትዮጵያችን እንደ ገናና ታሪኳ ሁሉ ጸንታ ትኖራለች ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.