Fana: At a Speed of Life!

ሀገር በጽናት እና በአንድነት በመጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ ማሻገር ወቅቱ የሚጠይቀው ሃላፊነት ነው -ብ/ጄ ካሳየ ጨመዳ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አባቶቻችን ከሀገር ውስጥ ባንዳና ከውጭ ጠላት ጠብቀው ያቆያት ሀገር በጽናት እና በአንድነት በመጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ ማሻገር ወቅቱ የሚጠይቀው ኀላፊነት ነው ሲሉ የቀድሞው ጦር ሠራዊት አባል ብርጋዴር ጄነራል ካሳዬ ጨመዳ ገለጹ።
ብርጋዴር ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሸን ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የውጭ ተልዕኮ ይዘው የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖችን ለማጥፋት ኢትዮጵያውያን በአራቱም ማዕዘን ሁሉንአቀፍ የትግል እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳለባቸው ገልጸዋል።
የሀገር ዳር ድንበር ጠባቂ እና ከፍተኛ መስዋእትነት እየከፈለ ያለውን የመከላከያ ሠራዊትን በሰው ኀይልና በቁሳቁስ ማጠናከር እንደሚገባም ገልጸዋል።
ብርጋዴር ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ አሸባሪው የትህነግ ቡድን እንዲከስም ሕዝቡ ወደ ግንባር በመዝመት እያሳዬ ያለውን ደጀንነት አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ነው የተናገሩት።
አሸባሪው የትህነግ ቡድን የከፈተው ጦርነትና ወረራ በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ መላው ኢትዮጵያውያን በአንድነት መታገል አለባቸው ነው ያሉት።
መስከረም 24 ቀን2014 የሚመሰረተው አዲሱ የኢትዮጵያ መንግሥት ሕግና ሥርዓትን በማስከበር፣ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ማኅበራትን በማካተት ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን እድገት እንዲሠራም ጠይቀዋል።
ጠንካራ ተቋማት እንዲገነቡም የኢትዮጵያ ሕዝብ በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ በንቃት መሳተፍ እንደሚገባውም ብርጋዴየር ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ ተናግረዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.