Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ መምህራን ትውልድ የመቅረፅ ሃላፊነታቸውን በንቃት እንዲወጡ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መምህራን ትውልድን የመቅረፅ ሃላፊነታቸውን በንቃት እንዲወጡ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ፕሬዚዳንቷ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር ለመምህራን እውቅና መስጠት ባህል መሆን እንዳለበት አንስተዋል፡፡

አያይዘውም መምህራን የነገ ትውልድ ተረካቢዎችን የሚያፈሩ የሙያ አባቶችና እናቶች በመሆናቸው ሊከበሩ እና ሊመሰገኑ እንደሚገባ ገልፀዋል።

መሰል እውቅና መሰጠቱም ሙያውን ወደ ሚገባው ከፍታ ቦታ ያስቀምጠዋልም ነው ያሉት።

ትምህርት ሚነስቴር ከመምህራን ማህበር ጋር በጋራ በመሆን “በቀውስ ውስጥም ሆነን ትውልድን እንቀርፃለን” በሚል መሪ ቃል የመምህራን ቀንን በሀገር አቀፍ ደረጃ ያከበረ ሲሆን፤ ለ183 ምስጉን መምህራን ሽልማት እና እውቅና ሰጥቷል።

በመርሃ ግብሩ የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያን ጨምሮ ሌሎች የሚኒስቴሩ የስራ ሃላፊዎች፣ መምህራን እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ብቃት ያላቸው መምህራንንና እጩ መምህራንን ለማበረታታት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

የመምህርነት ሙያ የሙያዎች ሁሉ መሰረት መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ በመላ ሃገሪቱ ያሉት መምህራን ክብር እና ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

ሀገር አቀፍ ውጤታማ የመምህራን የምስጋና እና እውቅና መስጠት መርሃ ግብርም በየዓመቱ እንደሚቀጥል መግለፃቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.