Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ ነገ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ በነገው እለት በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ኮንፈረንሱ ”ለሁላችንም የምትመች ኢትዮጵያን በጋራ እንፍጠር” በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄም ተነግሯል።

ኮንፈረንሱን ያዘጋጀው የኦሮሞ እና የአማራ የባለሃብቶች ኮሜቴ ነው።

ኮሜቴው ኮንፈረንሱን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፥ ኮንፈረንሱ በሀገሪቱ የሚፈጠሩ ችግሮችን በጠረጴዛ ዙሪያ በመነጋገር መፍታት እንደሚቻል ለማመላከት የተዘጋጀ ነው ብሏል።

“ይህ ኮንፈረንስ በመንግስት እየተሰራ ያለውን ሀገራዊ መግባባትን የመፍጠር እና በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም የማምጣት ጥረትን ለማገዝ የተዘጋጀ ነው” ሲሉም የኮሚቴው ሰብሳቢ ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው ገልጸዋል።

ኮንፈረንሱ 6 ሺህ ተሳታፊዎች የሚካፈሉበት እና በሚሊኒየም አዳራሽ የሚካሄድ ነው።

በኮንፈረንሱ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ወጣቶች እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች የሚሳተፉበት ይሆናል።

በምስክር ስናፍቅ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.