Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች አውደ ርዕይና ባዛር ተከፈተ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች አውደ ርዕይና ባዛር ተከፈተ፡፡

ባዛሩ “ሀገራዊ ጥሪ ለማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት’’ በሚል መሪ ቃል የተጀመረው፡፡

ሜክሲኮ በፌደራል አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ማስፋፊያ ባለሥልጣን ቅጥር ጊቢ ውስጥ ነው ባዛሩ የተከፈተው።

ባዛሩ ከታህሳስ 21 እስከ 27 ቀን ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚቆይ ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪው በማይናጋ መሰረት ላይ የተመሰረተ የኢኮኖሚ እድገት ለመመስረት የሚጫወተው ሚና እጅግ ከፍተኛ  መሆኑ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገቷን በማይናጋ መሰረት ላይ ለመጣል ለአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪው ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ባለስልጣን በማቋቋም ዘርፉን በሙያ፣ በዕውቀትና በገንዘብ በተደራጀ መልኩ በመደገፍ ኢኮኖሚያዊ አበርክቶውን ለማሳለጥ እየሰራች ትገኛለች ተብሏል፡፡

ባለስልጣኑ የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ ለማሳካት አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች እርስ በእርሳቸው በሙያ፣ በዕውቀትና ገንዘብ እንዲደጋገፉና ከከፍተኛና ዓለም አቀፍ አምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር በማስተሳሰር የእውቀት ሽግግርና የገበያ ትስስር በመፍጠር ኢኮኖሚ እድገቱን ለማሳለጥ በተለያየ ጊዜ አውደ ርዕይና ባዛር እያዘጋጀ እንደሚሰራ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

በዚህ ዓመትም በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዓለም አቀፍ አምራች ኢንዱስትሪዎች

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.