Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የጤና ተቋማት መሠረተ ልማት ግንባታ የ5 ወራት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሀገር አቀፍ የጤና ተቋማት መሠረተ ልማት ግንባታ የ5 ወራት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ዓለምጸሃይ ጳውሎስ፣ በሚኒስቴሩ የመሠረተ ልማት ዳይሬክቶሬት ሰራተኞች እና የሁሉም ክልሎች የዘርፉ ተወካዮች ተሳትፈዋል።
በውይይት ንግግር ያደረጉት ሚኒስትር ዴኤታዋ የጤና ዘርፉን አገልግሎት ጥራት ለማሳደግ የመሰረተ ልማት ግንባታ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
ለዚህም የጤና ዘርፉን ለማሳለጥ የሚገነቡ የጤና ተቋማት እና መሠረተ ልማቶች በተያዘላቸው ጊዜ ማጠናቀቅ ይገባል ነው ያሉት።
ሚኒስቴሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ወቅቱን የሚመጥን እና ነባራዊ ሁኔታውን ያገናዘበ የጤና መሠረተ ልማት ግንባታ ለማከናወን በትኩረት እየሰራ መሆኑንም አብራርተዋል።
የግንባታ ዕቃዎች መናር፣ የዲዛይን መሻሻል፣የበጀት እጥረት፣ በቅንጅት አለመስራት እና የወሰን ማስከበር የዘርፉ ዋና ተግዳሮቶች መሆናቸውን ተሳታፊዎች አንስተዋል።
አሁን ላይም ባለፍት አምስት ወራት የተከናወኑ የጤና ተቋማት እና መሠረተ ልማት ግንባታዎች አፈጻጸም ዙሪያ ምክክር እየተደረገ ይገኛል።
ዛሬ እና ነገ በሚካሄደው በዚህ የውይይት መድረክ በሁሉም ክልሎች ያለው የጤና ተቋማት እና መሰረተ ልማት ግንባታ አፈጻጸም የሚገመገም ይሆናል።
በመላኩ ገድፍ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.