Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የፓን አፍሪካ የትምህርት ቤቶች የእግር ኳስ ውድድር ተጀመረ

አዲስ አበባ ጥር 3፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ የፓን አፍሪካ የትምህርት ቤቶች የእግር ኳስ ውድድር በአዲስ አበባ ከተማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ተጀመረ።

የፖን አፍሪካ የትምህርት ቤቶች ውድድር ተተኪ ስፖርተኞችን ለመፍጠር ዕድል እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታዎች አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካ ሐሳብ ካመነጩት አገሮች አንዷ መሆኗ፣ ለአፍሪካ አገሮች ነፃነትና እኩልነት የበኩሏን ድርሻ የተወጣች እና የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት የአሁን የአፍሪካ ህብረት መስራችም መሆኗ ተገልጿል፡፡

የፓን አፍሪካ ትምህርት ቤቶች ውድድር መደረጉ በዲፕሎማሲ ግንኙነት የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ነው የተመለከተው።

የፓን አፍሪካ የትምህርት ቤቶች ውድድር በአገር አቀፍ ብቻ ሳይገደብ በአህጉር አቀፋ በሚደረጉ የትምህርት ቤቶች ውድድር ተሳትፎ እንደሚደረግም ተገልጿል።

የውድድሩ አላማ የአለም አቀፍ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን በአፍሪካ አህጉር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች በሆኑ ተማሪዎች መካከል በሁለቱም ፆታ ሀገራችንን በመወከል በየካቲት ወር በዲሞክራቲክ ኮንጐ ኪንሻሳ ላይ በሚደረገው የትምህርት ቤቶች ውድድር ላይ የሚሳተፉትን ለመለየት ነውም ተብሏል፡፡

ውድድሩ ከጥር 3-5/2014 ዓ.ም ለተከታታይ ለ3 ቀናት የሚካሄድ ይሆናልም ነው የተባለው፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.