Fana: At a Speed of Life!

ሁለተኛው የባለ ልዩ ጣዕም የቡና ውድድር ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ሁለተኛው የባለ ልዩ ጣዕም የቡና ውድድር ሊካሄድ መሆኑን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ ዛሬ ከኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ጋር በሰጠው የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ነው ውድድር ሊካሄድ መሆኑን ያስታወቀው፡፡

ውድድሩ በሦስት ደረጃዎች እንደሚካሄድና በብሔራዊ ባለሙያዎች፣ በዓለም አቀፍ ዳኞች፣ በዓለም ዓቀፍ የታወቁ የቡና ላboራቶሪዎች ተገምግሞ ማለፍ እንደሚኖርበት አስታውቋል፡፡

እንዲሁም አንድ ናሙና ከአንድ ማሳ እንደሚቀርብ የተገለጸ ሲሆን ከጥር 24 ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 3 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ናሙና መቀበል እንደሚጀምር ነው ባለስልጣኑ የገለጸው፡፡

ናሙናው ሦስት ኪሎ አረንጓዴ ቡና እና በተመሳሳይ ታጥቦ የተቀሸረ ሦስት ኪሎ ቡና መሆኑም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

ባለፈው አመት የዓለምን ክብረወሰን የሰበረ 1 ሺህ 462 ናሙና መሰብሰቡንም ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

መጀመሪያ በተካሄደው የልዩ ጣዕም ውድድር አማካኝነት አንድ ኪሎ ቡና 407 ዶላር መሸጡም ተገልጿል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ ውድድሩ የቡና ምርትና ምርታማነትን አሳድጎ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ ሚናው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.