Fana: At a Speed of Life!

ሁለት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰራተኞች ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰሜን አዲስ አበባ ዲስትሪክት ሰራተኞች የሆኑ ሁለት ግለሰቦች ከተገልጋይ 3 ሺህ ብር ጉቦ ሲቀብሉ በፖሊስ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ተቋሙ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ አሳውቋል፡፡
ሁኔታው የተከሰተው ለዲስትሪክቱ ከዚህ በፊት የመብራት ጥያቄ ያቀረበ የኢንዱስትሪ ባለቤት መኖሩን የተመለከተው አንደኛው ግለሰብ ከሌላ የተቋሙ የክሬን ሹፌር የሆነ ሠራተኛ ጋር በመመሳጠር በአጭር ጊዜ እናስገባልሃለን ብለው ገንዘብ እንዲሰጣቸው በማስማማታቸው መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ምንም እንኳ ደንበኛው አስፈላጊ ግብዓቶች እንዲሟሉለት አስቀድሞ ክፍያ ለተቋሙ የፈፀመና የመብራት መስመር ዝርጋታም እየተከናወነለት ቢሆንም ከተጠቀሰው ጊዜ በፊት እኛ የጎደለውን ግብዓቶች አሟልትን እናስገባልህ አንተም ገንዘብ ክፍለን በማለት ተደራድረው 3 ሺህ ብር ጉቦ ሊቀበሉ ሲመጡ ደንበኛው የፀረ-ሙስና ሰራተኞችንና ፖሊሶችን በመያዝ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።
ሰራተኞቹ አሁን በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳዩ በፍርድ ሂደት ላይ መሆኑም ታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሙስና ወንጀሎችና ብልሹ አሰራሮች የሚፈፅሙ የተቋሙ ባልደረቦችና ደላሎች ሲያጋጥም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ለሚመለከተው አካል ጥቆማ በማቅረብ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪውን ማቅረቡን ከፌደራል የስነምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.