Fana: At a Speed of Life!

‘‘ሁሉም ሴቶች ለብልጽግና፤ ብልጽግና ለሁሉም ሴቶች’’ በሚል መሪ ቃል ድጋፍ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ‘‘ሁሉም ሴቶች ለብልጽግና ፤ ብልጽግና ለሁሉም ሴቶች’’ በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ስታዲየም የሴቶች ድጋፍ እየተካሄደ ይገኛል።

በአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲን ወክለው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለአዲስ አበባ ምክር ቤት የሚወዳደሩ እጩዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም ከተገኙ ሴቶች ጋር ትውውቅ ያደርጋሉ።

በዛሬው እለት ከአዲስ አበባ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ሴቶች ለብልጽግና ፓርቲ ያላቸውን ድጋፍ እያሳዩ ይገኛሉ።

በመርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣ ሴት ሚኒስትሮች፣የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ አቶ መለሰ አለሙ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ ለህዝብ ተወካዮችና ለአዲስ አበባ ምክር ቤቶች እጩ የሆኑ የብልጽግና ፓርቲ ተወዳዳሪዎች ተገኝተዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ÷ ፓርቲው ለሁሉም የምትበቃ አዲስ አበባን እንዲሁም ለአለም ምሳሌ የምትሆንን ኢትዮጵያ ለመገንባት ይሰራል ብለዋል።

ለብልጽግና ፓርቲ እዚህ መድረስ የሴቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ÷ ብልጽግና የሴቶችን እኩልነት በወረቀት ብቻ ሳይሆን በተግባር ያሳየ ፓርቲ ነው ብለዋል።

ብልጽግና በራሱ ጥረት ብቻ ሳይሆን ህዝብን ይዞ፣ህዝብን አስቀድሞ ፣ ለዜጎች ክብርን እየሰጠ፣ የህዝብን ጥያቄ እየመለሰ ከህዝብ ጋር ሆኖ ሀገር ይገነባልም ነው ያሉት።

ፓርቲው ሰው ተኮር ስራዎችን እየሰራ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባዋ÷ አሁንም ቢሆን ጀመርን እንጂ አልጨረስንም ብለዋል።

በሃይማኖት እያሱ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.