Fana: At a Speed of Life!

ሃድያ ሆሳዕና ፌዴሬሽኑ ከሚሰጣችሁ ማናቸውም አገልግሎቶች ታገደ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃድያ ሆሳዕና የእግርኳስ ቡድን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከሚሰጣችሁ ማናቸውም አገልግሎቶች መታገዱ ተገለፀ፡፡
ፌዴሬሽኑ 15 የሃዲያ ሆሳዕና ተጫዋቾች ከሚያዚያ ወር ጀምሮ እስከ ውል ማብቂያቸው ድረስ ደመወዛቸውና ጥቅማ ጥቅማቸው እንዲከፈል መወሰኑን አስታውሷል፡፡
የእግርኳስ ቡድኑም ውሳኔውን ባለመቀበል ይግባኝ ቢጠይቅም የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ጉዳዩን በመመርመር ውሳኔውን በማፅደቅ በሰባት ቀን ውስጥ ክፍያ እንዲፈፀም ውሳኔ መሰጠቱ ይታወቃል፡፡
ሆኖም ተጫዋቾቹ ውሳኔው ተግባራዊ እንዳልተደረገላቸው አቤቱታ ማቅረባቸውን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚህም ሃድያ ሆሳዕና የእግርኳስ ቡድን የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔን ተግባራዊ እንዲያደርግ ቢጠየቅም ተግባራዊ ባለማድረጉ ፌዴሬሽኑ ከሚሰጣችሁ ማናቸውም አገልግሎቶች መታገዱ ታውቋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.