Fana: At a Speed of Life!

ሃገር አቀፍ የሞዴል ኢንተርፕራይዞች አውደ ርዕይና ባዛር በአዲስ አበባ ከተማ ተከፈተ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል የከተሞች የሥራ እድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ያዘጋጁት የገና በዓል ሃገር አቀፍ የሞዴል ኢንተርፕራይዞች አውደ ርዕይና ባዛር ተከፈተ፡፡

ባዛሩ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ እና የፌደራል የከተሞች የሥራ እድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረመስቀል ጫላ በተገኙበት በይፋ ተከፍቷል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር ዓባይ በዚህ ዐውደ ርእይ እና ባዛር ላይ ከ4 ሚሊየን በላይ ብር የገበያ ትስስር ይፈጠራል ብለዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የሚያደርገውን ድጋፍ በማጠናከር ሰፊ የገበያ እድል እንዲያገኙ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያመቻችም ገልጸዋል።

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ፥ ባዛሩ ከገበያ ትስስር ባለፈ ለወጣቶች እንደተሞክሮ የሚወሰድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ወጣቶችም ሥራ ሳይንቁ ባገኙት አጋጣሚ ተደራጅተው ለለውጥ እንዲተጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አውደ ርዕዩና ባዛሩ ከዛሬ ጀምሮ ለሰባት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ የግብርና ማቀነባበር ምርቶች፣ የዕደ ጥበብ ስራዎች የተሰማሩ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን እንደሚያቀርቡ ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.