Fana: At a Speed of Life!

ህብረተሰቡ በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ መረጃዎችን ትክክለኛነት በጥንቃቄ ማጣራት ይኖርበታል-  ብልፅግና ፓርቲ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ህብረተሰቡ ማንኛውንም ጉዳይ አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ መረጃዎችን ትክክለኛነት በጥንቃቄ ማጣራት ይኖርበታል አለ ብልፅግና ፓርቲ፡፡

ፓርቲው ባወጣው መግለጫ በአሁኑ ወቅት በመላው አለምም ሆነ በአገራችን በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ ሃሰተኛ ወሬዎች እየተበራከቱ ይገኛሉ ብሏል፡፡

ማንኛም ዜጋ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ መረጃዎችን ከመቀበሉ በፊት ከተረጋገጠና ከትክክለኛ ምንጭ የተገኙ መሆናቸውን በጥንቃቄ ማጣራት አለበት ብሏል ፓርቲው፡፡

ከሰሞኑ የፓርቲው ፕሬዚዳንትና የአገሪቱ ጠ/ሚኒስትር የሆኑትን የዶ/ር አብይ አህመድን ጤንነትና ደህንነት አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ የተናፈሰው ወሬ ፍጹም መሰረተ ቢስና ሆን ተብሎ ህብረተሰቡን ለማደናገር ሃላፊነት በማይሰማቸው አካላት የተሰራጨ ነውረኛ የሀሰት መረጃ ነው ሲል ገልጿል፡፡

ህዝቡ ለወደፊቱም ከተመሳሳይ ሀሰተኛ ወሬዎች መጠንቀቅ ይኖርበታል ሲል አሳስቧል፡፡

ህብረተሰቡን የማደናገርና ውዥንብር የመፍጠር ዓላማ ይዘው ሃሰተኛ ወሬዎችን እየፈበረኩ የሚያሰራጩ የጥፋት አካላትን በጥብቅ ተከታትሎ የህግ ተጠያቂ ማድረግ የመንግሥት ሃላፊነት ይሆናልም ብሏል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.