Fana: At a Speed of Life!

ህብረተሰቡ በግብይት ወቅት ለኮቪድ 19 ወረርሺኝ ከሚያጋልጡ ሁኔታዎች ራሱን መጠበቅ እንደሚገባው ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 27 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የገና በአል አስመልክቶ ህብረተሰቡ በግብይት ሂደት ለኮቪድ 19 ወረርሺኝ ከሚያጋልጡ ሁኔታዎች ራሱን መጠበቅና ከአላስፈላጊ መዘናጋቶች ራሱን መጠበቅ እንደሚገባው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገለጹ።
ሚኒስትሩ መልዕክቱን ያስተላለፉት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የኮቪድ 19 ወረርሺኝ መከላከያ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ድጋፍ ድርጊት መርሃ ግብር ላይ ነው።
አቶ መላኩ በወቅቱም በዓሉን አስመልክቶ በኢንዱስትሪዎች በርካታ ሰራተኞች እና በገበያ ቦታዎች በርካታ የግብይት ተዋንያኖች አሉ ብለዋል።
ስለሆነም እነዚህ ቦታዎች ለወረርሺኙ መስፋፋት ምክንያት በመሆናቸው ህብረተሰቡ በዓሉን ለማድመቅ በሚያደርጋቸው ማንኛውም እንቅስቀሴ ወቅት የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል።
ከዚያም ባለፈ በጤና ባለሞያዎች የሚሰጠውን መመሪያ በመተግበር ራሱን ከበሽታው በመከላከልና ለበሽታው ስርጭት መገታት በሚደረገው ጥረት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪያቸውን ማስተላለቻውን ከሚኒስቴሩ ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.