Fana: At a Speed of Life!

ህብረተሰቡ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን መቆሙንና አብሮነቱን ለመግለፅ በከፍተኛ ደረጃ ድጋፉን ቀጥሏል-ሰላም ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 12 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህብረተሰቡ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን መቆሙንና አብሮነቱን ለመግለፅ በከፍተኛ ደረጃ ድጋፉን መቀጠሉን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።
ድጋፉን የሚያስተባብር ብሄራዊ የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ በሰላም ሚኒስቴር ሰብሳቢነት መቋቋሙ ይታወሳል።
በዚህም መሰረት ዛሬ ብሄራዊ ኮሚቴው ባደረገው ስብሰባ ሰራዊቱን ለመደገፍ የህብረተሰቡ ተሳትፎና እንቅስቃሴ እጅግ አበረታች መሆኑን ገልጸዋል።
ስብሰባውን ተከትሎ የሰላም ሚኒስቴር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ÷ በኮሚቴው አስተባባሪነት ከደም ልገሳ አንስቶ እስከ ከፍተኛ መጠን ያለው በገንዘብና በአይነት ድጋፍ ባለፉት 10 ቀናት ውስጥ መሰባሰቡን ተናግረዋል።
ለድጋፉም በብሄራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው በመከላከያ ሰራዊታችንና በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ስም ልባዊ ምስጋና አቅርበው÷ድጋፉም ተጠናክሮ እንዲቀጥል መልእክት ማስተላለፋቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.