Fana: At a Speed of Life!

ህብረተሰቡ የመለያ ቁጥሩ 003-100 የሆነውን የጄኖቪያን ፍራፍሬና ለውዝ እንዳይጠቀም ባለስልጣኑ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ህብረተሰቡ የመለያ ቁጥሩ 003-100 የሆነውን የጄኖቪያን ፍራፍሬ እና ለውዝ የተባለ ስናክ ምግብ ምርት እንዳይጠቀም የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳሰበ፡፡
የአለም አቀፍ የምግብ ደህንነት ማስጠንቀቂያ ተቋም ፋብሪካውን ዋቢ አድረጎ ለኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በማለከው መረጃ መሠረት÷ የጄኖቪያን ፍራፍሬ እና ለውዝ የተባለ ስናክ ምግብ ምርት ሊስቴሪአ ሞኖሳይቶጅን በተባለ ጎጂና ገዳይ ተህዋስያን መበከሉ ተረጋግጧል፡፡
በመሆኑም ህብረተሰቡ የመለያ ቁጥሩ 003-100 የሆነውን እንዲሁም የተመረተበት ቀን ቤስት ቢፎር ጃኗሪ 12 2023 የሆነ የምግብ ምርት እንዳይጠቀም ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡
ከባለስልጣኑ ፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው÷ ማንኛውም የህረተሰብ ክፍልና የሚመለከተው አካልም ከላይ የተገለፀውን ምርት ሲያገኝ በስልክ ቁጥር 8482 እና በአካባቢ ለሚገኝ ተቆጣጣሪ አካል በመጠቆም እንዲተባበር የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ጥሪ አቅርቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.