Fana: At a Speed of Life!

ህብረተሰቡ የኢሬቻ በዓልን በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት እንዲያከብር አባ ገዳዎች አሳሰቡ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኦሮሞ ወጣት የኢሬቻ በዓልን በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት እንዲያከብር አባገዳዎች አሳስበዋል፡፡
የኦሮሞ የአባገዳዎች ህብረት በሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ ክብረ በዓል አከባበር ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫው በኮቪድ 19 ወረርሽኝ እና የወቅቱ የጸጥታ ሁኔታ ምክንያት የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ ክብረ በዓል በውስን ሰው እንዲከበር መወሰናቸውን አባገዳዎቹ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ህብረተሰቡም እራሱን እና ቤተሰቡን ከኮቪድ 19 በመጠበቅ በአባ ገዳዎች ህብረት በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በዓሉን እንዲያከብር አባገዳዎቹ አሳስበዋል፡፡
እንዲሁም የኢሬቻ በዓል የሰላም ፣ የፍቅር እና የምስጋና በዓል ነው ያሉት አባ ገዳዎቹ መላው የኦሮሞ ወጣት በዓሉን ከፖለቲካ በጸዳ መንገድ እንዲያከብር ጥሪ ማስተላለፋቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.