Fana: At a Speed of Life!

ህንድ ፈጣን የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ሰራች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህንድ ፈጣን የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ሰርታለች፡፡

ሃገሪቱ የሰራችው መመርመሪያ ልክ እንደ እርግዝና መመርመሪያ ውጤቱን በፍጥነት ሊያሳይ የሚችል ነው ተብሏል፡፡

በዚህም ከአንድ ሰዓት በታች በሆነ ጊዜ ውስጥ ውጤቱን እንደሚያደርስ ነው የተነገረው፡፡

በ2 ሺህ ህሙማን ላይ ምርመራ ተደርጎም ውጤታማነቱ መረጋገጡ ተገልጿል፡፡

ፌሉዳ የተባለው ይህ መመርመሪ ኪት ዋጋው 500 የህንድ ሩፒ ወይም ሰባት ዶላር አካባቢ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የህንድ መንግስት ዋና የሳይንስ አማካሪ ፕሮፌሰር ኬ ቪጃይ ራጋቫን እንዳሉትም “ሙከራው ቀላል ፣ ትክክለኛ፣ አስተማማኝ እና ወጪ ቆጣቢ ነው ፡፡

ህንድ በአሁኑ ጊዜ ከ1 ሺህ 200 በላይ ላቦራቶሪዎች ያሏት ሲሆን በቀን 1 ሚሊየን ናሙናዎችን እየመረመረች ትገኛለች፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.