Fana: At a Speed of Life!

ህወሃቶች እንዳይገድሉን ፈርተን በግዳጅ ወደ ጦርነት እየተማገድን ነው -የተማረኩ ህጻናት ወታደሮች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “ህወሃቶች እንዳይገድሉን ፈርተን በግዳጅ ወደ ጦርነት እየተማገድን ነው” ሲሉ በሀገር መከላከያ የተማረኩ ህጻናት ወታደሮች ተናገሩ።
የኢዜአ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ህጻናት አሸባሪው የህወሃት ቡድን አስገድዶ ወደ ጦርነት እየማገዳቸው መሆኑን የሚናገሩት በእንባ ታጅበው ነው።
ከእነዚሁ ታዳጊ ህጻናት ወታደሮች መካከል ኢየሩሳሌም ሃይላይ አንዷ ናት፤ እየሩሳሌም ሐምሌ 7 ቀን 2013 ከመቀሌ በድንገት ከቤቷ እንደወጣች ታፍና ወደ ጦርነት መምጣቷን ትናገራለች።
ምንም ዓይነት ሥልጠና ሆነ መሣሪያ ሳታገኝ ”አሸንፈን አዲስ አበባ እንገባለን” በሚል ባዶ የተስፋ ቃል እየሸነገሉ ወደ ጦርነት እንዳስገቧቸውም ትገልጻለች።
በመጨረሻም ጦርነቱ ሲጀመር እንደ የዕድሜ እኩዮቿ ህጻናት “ደንግጠን ራሳችንን ለማዳን ለመከላከያ ሠራዊት እጃችንን ሰጥተናል” ትላለች ኢየሩሳሌም።
ሌላዋ ህጻን ሄለን ሀድጉ በበኩሏ ከመቀሌ በመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ መሥመር አቅጣጫ አምጥተው አፋር ክልል እስከሚገቡ ድረስ ወዴት እየወሰዷቸው እንደሆነ ሳታውቅ መቆየቷን ታስታውሳለች።
በጦርነት ውስጥ ደረቅ ብስኩትና የወንዝ ውሃ እየጠጡ መቆየታቸውን የምትናገረው ሄለን፣ “ጓደኞቼ ራሳቸዉን ለማትረፍ በጭንቅ ላይ በነበሩበት ወቅት በአገር መከላከያ ተማርኬ ሕይወቴ በመትረፉ ተደስቼያለሁ” ብላለች።
የትግራይ ሕዝብ የህወሓት አሸባሪ ቡድን ራሱን በሥልጣን ላይ ለማቆየት ህጻናትን በግፍ ወደ ጦርነት በመማገድ እየፈጸመ ያለውን ግፍ እንዲያቆም እንዲታገለውም ጠይቃለች።
ሌላው ህጻን ኢሳያስ ዓለም በበኩሉ ጁንታዉ የትግራይ ህጻናትን በግዳጅ ወደ ጦርነት እየማገዳቸው መሆኑን ይመሰክራል።
እሱን ጨምሮ ሌሎች የእድሜ እኩዮቹ ተምረው ነገ የተሻለ ዜጋ ለመሆን ፍላጎትና ህልማቸው ቢሆንም፤ጁንታው እንዳይገላቸው በመፍራት በተዋጊነት መሰለፋቸውን ይናገራል።
በጁንታው ተገድደው ወደጦርነት የገቡትና በመከላከያ ሰራዊት ጥንቃቄ የተሞላበት ርምጃ ህይወታቸው ተርፎ የተማረኩት ህፃናት “የጁንታው አመራሮች የራሳቸዉን ልጆች በውጭ አገር እያስተማሩ የእነሱና የቤተሰቦቻቸው ሕይወት ተስፋ በመደብዘዙ ተቆጭተናል” ይላሉ።
ህፃናቱ፣ የትግራይ ሕዝብ ራሱን በሥልጣን ለማቆየት ሲል ህጻናትን በግፍ ወደ ጦርነት የሚማግደውን አሸባሪው የህወሃት ቡድን ሊታገለው እንደሚገባ ነው በአፋር ግንባር በሀገር መከላከያ ሰራዊት የተማረኩተ ህጻናት ወታደሮች የገለጹት።
ጁንታዉ በኢትዮጵያ ላይ በጀመረዉ አጥፍቶ መጥፋት ዘመቻ፣ የትግራይ ህጻናትና ሴቶችን በተዋጊነት መጠቀም ከጀመረ ሰነባብቷል።
የሰሞኑን በአፋር ክልል ፈንቲ-ረሱ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች በከፈተዉ ጥቃት የተማረኩት እነዚሁ ህጻናት፣ የጁንታው አሳፋሪና ከሰብዓዊነት የወጣ ባህሪን ዓለም በትኩረት ሊያየው እንደሚገባም ተናግረዋል።
የአፋር ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሺን ምክትል ኮሚሽነር መሀመድ አህመድ እንደገለጹት ጁንታው በዞኑ ያደረገዉን ወረራ የአፋር አርብቶ አደር ከመከላከያ ሠራዊትና ልዩ ሃይል ጎን በመቆም እየደመሰሰዉ ነዉ።
ጁንታዉ ዛሬ በሀገር ላይ የከፈተዉ ጥቃት የቆየ ሀገር የማፍረስ ህልሙን እውን ለማድረግ በግልጽ የጀመረው መሆኑን ገልፀዋል።
በጦርነቱም ህጻናትን በሃሺሽ አስክሮ በማስገባት በተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆኖ ከማንም በላይ የትግራይ እናቶችና ህጻናት ጠላትነቱን እያስመሰከረ ነዉ”ብለዋል።
በመሆኑም የትግራይ ህዝብ ራሱን ለማቆየት ህፃናትን በጭካኔ ወደ ጦርነት እየማገደ ያለውን አሸባሪ ቡድን፣ ከመከላከያና ከሌላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ጎን በመቆም እንዲታገለው ጠይቀዋል።
አሸባሪው ህወሃት ለአቅመ አዳም እና ሔዋን ያልደረሱትን ህጻናት እያስገደደ ለሦስት ቀናት ያልበለጠ ሥልጠና በመስጠት ወደ ውጊያ አስገብቶ መቋቋም በማይችሉት ጦርነት እየማገዳቸው መሆኑን ነው መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ገልጿል።
““በጦር ሜዳ ካሰለፋቸው ህጻናት ድል አገኛለሁ ብሎ በማሰብ እያስጨረሳቸው ይገኛል” ያለው ሚኒስቴሩ÷ ይህ ሳይበቃ በውጊያ የተገደሉትን ህጻናት ሬሳ በመሰብሰብ “የኢትዮጵያ መንግስት ሠራዊት ገደላቸው” ብሎ በውጊያ ያስጨረሳቸውን ህጻናት ሬሳ መነገጃ ለማድረግ የተለመደውን የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ በማሰራጨት ሬሳቸውን ኹሓ ላይ ሰብስቦ እንደሚገኝ ጠቁሟል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
52
Engagements
Boost Post
42
2 Comments
8 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.