Fana: At a Speed of Life!

ህወሓት ሰብዓዊ እርዳታን ከንጹሀን ቀምቶ በመውሰድ ልምድ ያለው ድርጅት ነው- የቀድሞ የአውሮፓ ዲፕሎማት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ህወሓት በጦርነቱ ምክንያት የተቸገሩ ዜጎችን ለመደገፍ ወደ ትግራይ የሚላከውን ሰብዓዊ እርዳታ የመቀማት ልምዱን አጠናክሮ መቀጠሉን የቀድሞ የአውሮፓ ዲፕሎማት ተናገሩ።
የኢትዮጵያን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተሉትና በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር የነበሩት ሲሞ ፓርቪያነን እንደገለጹት÷ ህወሓት ለወታደራዊ ግጭቶች ረሀብን እንደ መሳሪያ የሚጠቀም ድርጅት ነው።
ህወሓት በ1980ዎቹ ሲያደግ በነበረው የትጥቅ ትግል ወቅትም ይህን ተግባር መፈጸሙን አስታውሰዋል።
አሁንም ቢሆን ህወሓት ሴቶችን፣ ሕጻናትንና አዛውንቶችን ለመታደግ ወደ ክልሉ የሚላኩ ሰብዓዊ እርዳታዎችን እየቀማ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በወቅቱ በ1977 ዓ.ም በረሃብ በተጎዱ ወገኖች ስም ከተገኘ 100 ሚሊየን ዶላር ውስጥ 95 በመቶውን ለትጥቅ ትግሉ እንዳዋለውም ነው ያስታወሱት፡፡
ዲፕሎማቱ የኢትዮጵያ መንግስት የተኩስ አቁም አውጆ ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ክልሉ እንዲገባ ማድረጉ÷ ህወሓት የተዛባ መረጃ እንዳያሰራጭ አድርጎታል ብለዋል።
ህወሓት ምግብ ብቻ ሳይሆን ከ1 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች፣ ነዳጅና መድሃኒቶችን ጭምር ወስዶ ለተዋጊዎቹ መስጠቱንና ለግጭት ማስፋፊያ መጠቀሙን ተናግረዋል።
ይህ ብቻ ሳይሆን ህወሓት ሁሌ ራሱንና የትግራይን ሕዝብ ተበዳይ የሚያስመስል ፕሮፓጋንዳ የሚያናፍስ ድርጅት እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
ዲፕሎማት ሲሞ መደበኛ÷ መገናኛ ብዙኃን የህወሓትን የተሳሳቱ መረጃ የሚያጋልጡ ስራዎችንና በአፋርና አማራ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ መረጃ መስጠት እንዳለባቸውም አመላክተዋል።
አሸባሪው ህወሓት በ1977 ዓ.ም ለረሃብ የተጋለጡ ዜጎችን ለመድረስ በሚል ያገኘውን የእርዳታ ገንዘብ እህል ገዝቼበታለሁ በማለት ማጭበርበሩን የቀድሞ አባላቱ እንዳጋለጡ ከ12 ዓመታት በፊት ቢቢሲ መዘገቡ ይታወቃል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.