Fana: At a Speed of Life!

ህወሓት በኦነግ ሸኔ አማካኝነት በኦሮሚያ ክልል ሊፈጽም የነበረው ጥቃት ከሽፏል – የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ህወሓት በኦሮሚያ ክልል አቅዶት የነበረው ትርምስ እንደ ፍላጎቱ አለመሳካቱን የክልሉ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር እና የኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ ሐላፊ ጌታቸው ኢታና ገለፁ።

ከሓዲው የጁንታ ቡድን በሠራዊቱ ላይ ጥቃት ከፈፀመ በኋላ በኦነግ ሸኔ አማካኝነት የኦሮሚያ ክልልን ለማተራመስ ብሎም የሀገሪቱን ህልውና አደጋ ላይ ለመጣል የነበረው እቅድ በህዝቡ ፣ በጀግናው መከላከያ ሠራዊት ፣ የክልሉ ልዩ ሐይል ፣ መደበኛ ፖሊስ እና ሚሊሻ በቅንጅት መክሸፉን አረጋግጠዋል።

መከላከያ ውድ ዋጋ ከፍሎ ሀገሩን ከሴረኞች እኩይ ዓለማ ማትረፍ በመቻሉ ክብርና ምስጋና ይገባዋል ያሉት ሐላፊው፤ ወደፊትም በክልሉ አንዳንድ አከባቢዎች ተደብቀው የሚንቀሳቀሱትን ርዝራዦችን ለማስወገድ ከመከላከያ ጋር በጥምረት መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ትህነግ ለፀረ ሠላሙ ኦነግ የስልጠናና የሎጅስቲክስ ድጋፍ ይሰጥ እንደነበር የገለፁት ደግሞ የክልሉ ፖሊስ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ምክትል ኮሚሽነር ሙላት ወርዶፋ ናቸው።

ሠራዊቱ በህልውና ዘመቻ ላይ በነበረበት ወቅትም ሆነ በቅርብ ጊዜያት በጠላት ላይ በተወሰደው እርምጃ ለኦነግ ስልጠናና የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርጉ የነበሩ በርካታ የህወሃት አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋልም ብለዋል ።

ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ ፀረ ሠላም ኃይሎች መደምሰሳቸውንና የጦር መሣሪያዎች መማረካቸውንም ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.