Fana: At a Speed of Life!

ህወሓት በከፈተው ጦርነት ምክንያት የመስህብ ስፍራዎችና የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ከ67 ሚሊየን ብር በላይ ማጣታቸው ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ በጦርነቱ ምክንያት ከጎብኚዎች ያገኝ የነበረውን 7 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ማጣቱን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ሰላማዊት ካሳ በሰጡት መግለጫ፥ የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ በጦርነቱ ምክንት የጎብኚ ፍሰቱ ሙሉ ለሙሉ በመቆሙ ምክንያት ሊያገኝ የሚችለውን 7 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ማጣቱን ገልፀዋል፡፡
በዋናነትም ኑሮውን በጎብኚዎች ላይ ያደረገው የአካባቢው ነዋሪ 36 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገቢ አጥቷል ብለዋል ሚኒስትር ዲኤታዋ፡፡
ይህም ማህበራዊ ቀውስ እንደሚያስከትል ይታወቃል ያሉት ሚኒስትር ዲኤታዋ፥ መላው ኢትዮጵያዊ እና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት እንቅስቃሴ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል የተለያዩ ጥብቅ የማህበረሰብ አካባቢዎች በሽብርተኛው ህወሓት ጉዳት እንደረሰባቸው አንስተዋል።
ከእነዚህም ውስጥ የመንዝ ጓሳ የማህበረሰብ ጥብቅ ስፍራ፣ የቦረና ሳይንት ወረሂመኑ ብሄራዊ ፓርክና የጉና እና የአቡነ የሴፍ የማህበረሰብ ጥብቅ ስፍራን ለአብነት ጠቅሰዋል፡፡
በተጨማሪም በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር በቅርስ፣ እምነትና የመስህብ ስፍራዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ያነሱት ሚኒስትር ዲኤታዋ፥ እስካሁን በባለሙያ በተደረገ ልየታ በ6 የሃይማኖት ተቋማት፣ 22 የቱሪዝም አገልግሎት መስጫ እና ሁለት የባህል ተቋማት ላይ ውድመት መድረሱን አስረድተዋል።
በላስታ ላል ይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ላይ የደረሰው ጉዳትም ዝርዝር ጥናት ይደረግበታል ነው ያሉት።
በእነዚህና ሌሎች አካባቢዎች የደረሰው ጉዳትም ተጨማሪ ጥናት እየተደረገ ለህዝቡ ይፋ እንደሚደረግም ተገልጿል፡፡
በተመሳሳይ በአፋር ክልል በባህላዊ ፣ በእምነት ተቋማት፣ በተፈጥሮ ሃብቶች እንዲሁም በመሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት መድረሱ የተገለፀ ሲሆን፥ ይህም ተጨማሪ ሰፊ ጥናት የሚያስፈልገው መሆኑን ጠቁመዋል።
በክልሉ ተመሳሳይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፥ ከቱሪም ዘርፍ ይገኝ የነበረው 25 ሚሊየን ብር በጦርነቱ ምንክንያት አለመገኘቱን ነው የገለጹት።
በመስህብ ስፍራዎች ላይ በገንዘብ ሊተመኑ ከሚችሉ ቁሳዊ ጉዳቶች ባለፈ ማህበረሰቡ ላይ ጥልቅ ሆነ የስነልቦና ጉዳት ደርሷል ብለዋል ሚኒስትር ዲኤታዋ በመግለጫቸው፡፡
ለታሪካዊ ቅርሶች ጥገና ለማድረግ የፈረንሳይ መንግስትን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ተቋማት ቃል መግባታቸውንም ጠቁመዋል።
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህንንም ሆነ ማህበረሰቡ ላይ የደረሰውን የገቢ ምንጭ ጉዳት በመረዳትም ሌሎች ግንባሮች ላይ ያደረገውን ተጋድሎ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.