Fana: At a Speed of Life!

ህወሓት በዋድላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከ42 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ውድመት አድርሷል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት ከ42 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የንብረት ዘረፋና ውድመት መፈጸሙን በሰሜን ወሎ ዞን የዋድላ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ፋንታሁን አስታወቁ፡፡

 

የሽብር ቡድኑ በወረዳው በነበረው ቆይታ በሆስፒታሉ ላይ ከፍተኛ የንብረት ዘረፋና ውድመት መፈጸሙንም ነው ሥራ አስኪጁ ያብራሩት፡፡

ሆስፒታሉ ከ200 ሺህ በላይ ለሆኑ ሰዎች አገልግሎት የመስጠት አቅም የነበረው ሲሆን÷ አሁን ላይ በአሸባሪው ህወሓት 42 ሚሊየን 500 ሺህ ብር የሚገመት የንብረት ዘረፋና ውድመት ስለተፈጸመበት ምንም አይነት አገልግሎት መስጠት የማይችልበት ደረጃ ላይ ነው ብለዋል ሥራ አስኪያጁ፡፡

በዚህም ድንገተኛና ተከታታይ ህክምና የሚፈልጉ ዜጎች እየሞቱና በበሽታ እየተሰቃዩ ነው መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

ሆስፒታሉ ወደ መደበኛ ስራው ተመልሶ በበሽታ የሚሰቃዩ ዜጎችን ለመታደግ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ አቶ ተስፋዬ ፋንታሁን ጥሪ ማቅረባቸውን ከመቄት ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.