Fana: At a Speed of Life!

ህወሓት የአፋር ነፃ አውጪን በመጠቀም ወደ ጂቡቲ ለመሻገር የወጠነው እቅድ ከሽፏል- አቶ አወል አርባ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሕግን በማስከበር ዘመቻ ወቅት መከላከያ እና የአፋር ክልል በመቀናጀት ባደረጉት ስምሪት በጁንታው ላይ ድልን መቀዳጀት መቻላቸውን የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል ዐርባ  ገለፁ፡፡

ሕወሓት ለጥፋት ዓላማው ማስፈፀሚያ ከአንድ ዓመት በላይ ሲያሰለጥንና ሲያስታጥቀው የነበረውንና ራሱን የአፋር ነፃ አውጪ ብሎ የሚጠራውን ኡጉጉሙ፤ ወደ ሠላም ፣ ድርድርና ልማት ማስገባት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ጁንታው ኡጉጉሙን በመጠቀም ወደ ጂቡቲ ለመሻገር የወጠነው እቅድ ሊከሽፍበት ችሏል ብለዋል፡፡

የመከላከያ መረጃና የአፋር ክልል ይህንን ሴራ አስቀድመው በመረዳት በፍጥነት አካባቢውን ባይቆጣጠሩት ኑሮ ፣ ኡጉጉሙን በመጠቀም የጁንታው አመራሮች በቀላሉ ወደ ጅቡቲ ማምለጥ ይችሉ እንደነበር ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.