Fana: At a Speed of Life!

ህዝቡ፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና መንግስት በጋራ ቆመን ጠላቶቻችን የምናሸንፍበት ጊዜ ላይ ነን – የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ህዝቡ፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና መንግስት በጋራ ቆመን ጠላቶቻችን የምናሸንፍበት ጊዜ ላይ ነን አሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር::
የአማራ ምሁራን መማክርት ጠቅላላ ጉባኤውን ዛሬ በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው፡፡
በጉባኤው ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር የአማራ ህዝብ ጠላቶች ስንጥቅ እየፈለጉ በጋራ እንዳንቆም እየሰሩብን ነው ብለዋል፡፡
ጠላቶቻችን በጎጥና በመንደር እየከፋፈሉ መከራችንን ለማብዛት ይፈልጋሉ ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ ህዝቡ፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና መንግስት በጋራ ቁመን ጠላቶቻችን የምናሸንፍበት ጊዜ ላይ ነንም ብለዋል፡፡
በመካከላችን ያለው የፖለቲካ አመላካከትና ርዕዮት አለም ሳይገድበን በህዝባችን መሰረታዊ ጥያቄዎችና በጋራ እየተፈተንባቸው ባሉ አጀንዳዎች ላይ መግባባት አለብን ጊዜውም አሁን ነው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
“ላንጨርስ አልጀመርንም የጀመርነውን በድል እንጨርሳለን” ምሁራን ከዳር ተመልካችነት ወጥተውና ከአስፈጻሚው አካል ጋር መገፋፋቱን ትተው የህዝቡን ችግሮች ከነመፍትሄዎቻቸው በጥናት ሰንደው በማቅረብ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡም ርእሰ መስተዳደሩ አሳስበዋል፡፡
የመማክርቱ ሰብሳቢ ገበያው ጥሩነህ (ዶ.ር) የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ ለህዝብና ሀገር የሚጠበቅበትን ለመወጣት እየሰራ ያለ ተቋም ነው ብለዋል፡፡
ለስራዎቹ ስኬታማነትም የመንግስት አስፈጻሚ አካላትና ምሁራን በጋራ መስራት እንደሚገባቸው ገልጸዋል፡፡
መማክርቱ ለህዝቡ የሚበጁ ሀሳቦችን በማደራጀት ለተግባራዊነታቸው እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ አብመድ ዘግቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.