Fana: At a Speed of Life!

ህግ ማስከበርና ህልውና ዘመቻ ወቅት በትግራይ ክልል ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ አባ ገዳዎች እና ሀዳ ሲቄዎች መቀሌ ገቡ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህግ ማስከበርና ህልውና ዘመቻ ወቅት በትግራይ ክልል ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ አባ ገዳዎች እና ሀዳ ሲቄዎች መቀሌ ገብተዋል።
የኦሮሞ አባገዳዎች እና ሀዳ ሲቄዎችም መቀሌ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር ሰብሳቢ ዶክተር ሙሉ ነጋ እና ሌሎች የክልሉ አመራሮችን ጨምሮ የሀይማኖት አባቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ልዑኩም ከኦሮሚያ ክልል ሁሉም ዞኖች ህዝቡ በራሱ ፍላጎት ለወንድም እና እህት የትግራይ ህዝብ ያሰባሰበውን ድጋፍ ነው የሚያስረክበው።
የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎችም ለልዑካን ቡድኑ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በአፈወርቅ አለሙ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.