Fana: At a Speed of Life!

ህፃናት ልጆችን ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በኢትዮጵያ እስከ አሁን 64 ሺህ 301 ያህል ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን ከእነዚህም ወስጥ 644 የሚሆኑት ከ 0 እስከ 4 አመት ያሉ ሕፃናት ሲሆኑ 788 ያህሉ ደግሞ ከ 5 እስከ 14 አመት ያሉ ሕፃናት ልጆች ናቸው፡፡

ህፃናት ልጆችም በኮሮና ቫይረስ ተይዘው እንደ አዋቂዎች ምንም የህመም ስሜቶች ወይም ቀላል የህመም ስሜቶች ሊያጋጥማቸው ሲችል ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የመግባታቸው እድል ግን ዝቅ ያለ ነው ተብሏል፡፡

በብሔራዊ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል የኮቪድ-19 የህክምና አገልግሎት ተቋማት ዝግጅት እና የቤት ውስጥ ራስን ለይቶ ህክምና  እንክብካቤ ክፍል ሀላፊ አቶ ሄኖክ ሀይሉ  እንደተናገሩት፤የኮሮና ቫይረስ ከጨቅላ ህፃናት ጀምሮ የሚይዝ በሽታ ሲሆን ህፃናቱ ምንም አይነት የህመም ምልክት ላያሳዩ ወይም ቀለል ያለ የህመም ምልክቶች ሊኖራቸው ቢችልም ወደ ሌላው የማህበረሰብ ክፍል ግን ቫይረሱን ያስተላልፋሉ፡፡

በዚህም ህፃናት ልጆች በሽታን የመከላከል አቅማቸውን ለማጎልበት ቤተሰቦች አቅማቸው በሚችለው መጠን ለልጆቻቸው የተመጣጠነ ምግብ ቢመግቡ ተመራጭ ነው፡፡

በሌላ መልኩ ተጎዳኝ ህመም ላለባቸው ልጆች ልዩ እንክብካቤ ማድረግ ይገባቸዋል ፡፡

ልጆች በአሁኑ ሰዓት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ ወደ ውጪ ወጥተው መጫወት ስለማይችሉ ወደ ትምህርት ቤት ስለማይሄዱ፣ጓደኞቻቸውጋር ስለማይገናኙ ጭንቀት፣ድብርት እና የተለያዩ የባህሪ ለውጥ ሊያሳዩ ይችላል፡፡

ስለሆነም በቤት ውስጥ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ቀለል ያለ ጤንነታቸውን እንዲሁም በአጠቃላይ የህፃናቱን ሁኔታ ያገናዘበ የቤት ውስጥ ስራዎችን በመስራት፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ፣የተመጣጠኑ ምግቦችን በመመገብ ይሄን ጊዜ ማሳለፍ እንዳለባቸው ገልፅዋል የተለየ የህመም ስሜት እንደ ሳል ትኩሳት፣የአየርማጠር፣ቶሎቶሎ የመተንፈስ እና ሌሎች የበሽታ ምልክቶች ከታየባቸው ወደ ጤና ተቋማት መውሰድ እና አስፈላጊውን የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

ህፃናት በቂ የቀጥታ የፀሀይ ብርሀን እንዲያገኙ ማድረግ ፣ የእናት ጡት ወተት እስከ 2 አመት ድረስ (ከ6 ወር በኃላ ከተጨማሪ ምግብ ጋር) መመገብ ፣የክትባት ጊዜያቸውን በጠበቀ መልኩ እና በተለያየ ጊዜ ለተላላፊ በሽታዎች ማስከተብ የሚኖርብንን ክትባት እንዲያገኙም ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

በዚህ ወቅት  ህፃናት ልጆችን ይዞ ከቤት መውጣት ግዴታ ከሆነው ከሁለት አመት በላይ ለሆኑ ህፃናት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያወልቁ፣የእጃቸውን ንፅህና እየጠበቅን ርቀታቸውን መጠበቅ አስፈላጊ እንደሆነ ከህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.