Fana: At a Speed of Life!

ሆንግ ኮንግ ለዜጎቿ የኮሮና ቫይረስ የምርመራ ዘመቻ ማድረግ ጀመረች

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሆንግ ኮንግ ለዜጎቿ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ዘመቻ ማድረግ ጀመረች።

የራስ ገዝ አስተዳደሯ ሆንግ ኮንግ በፍቃደኝነት ላይ ተመስርታ የምታደርገው ምርመራም ከቻይና በመጡ የህክምና ባለሙያዎች በመታገዝ የሚደረግ ነው ተብሏል፡፡

በዚህም ከ7 ነጥብ 1 ሚሊየን ህዝቧ ውስጥ ከቅዳሜ ጀምሮ 500 ሺህ ሰዎች የቫይረሱን ምርመራ ለማድረግ መመዝገባቸው ተነግሯል።

ነገር ግን አንዳንድ የፖለቲካ ሰዎች ቻይና ግለሰቦችን ለመከታተል የዲ ኤን ኤ ናሙናዎችን ልትሰበስብ ትችላለች የሚል ስጋት እንዳላቸው ሲናገሩ አንዳንድ የጤና ባለሙያዎች ደግሞ ጥረቱን ውጤታማ ያልሆነ የሀብት ብክነት ነው ሲሉ ተችተዋል፡፡

ሆኖም ይህ የፓለቲከኞች ትችች ተቀባይነት እንዳላገኘ እየተነገረ ይገኛል።

የምርመራ ዘመቻው የቫይረሱን ስርጭት ለማወቅ እና ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ይረዳል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

በሃገሪቱ እስካሁን 5 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ቻይና እና ሩሲያ ትምህርት ቤቶቻቸውን መክፈት መጀመራቸው ታውቋል፡፡

በሩሲያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን በላይ የደረሰ ቢሆንም በሃገሪቱ የሚገኙ ኮሌጆች እና ሌሎች ትምህርት ቤቶች በአዲሱ የትምህርት ዘመን ይከፈታሉ ነው የተባለው፡፡

እንዲሁም በቻይናዋ ውሃን ከተማ የሚገኙ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለሳቸው ታውቋል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.