Fana: At a Speed of Life!

ለሀገር ክብር ሲሉ ውድ ህይወታቸውን በመስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖች ምስጋና ይገባል- አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለሀገር ክብር ሲሉ ውድ ህይወታቸውን በመስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖች ምስጋና ይገባል አሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ብሔራዊ የደህንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው።

አቶ ገዱ የህግ የበላይነት ዘመቻ ድልን አስመልክተው የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክትም ኢትዮጵያዊነት አሸንፏል ብለዋል።

ክብርና ሞገስ ለመከላከያ ሰራዊትና ለሃገራቸው ክብር ሲሉ ውድ ህይዎታቸውን በመስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖቻችን ሲሉም አመስግነዋል።

የአማራ፣ የአፋርና የሌሎችም ልዩ ሃይል እና ሚሊሻ አባላት የእኛ መኩሪያዎቾ ናችሁና እጅ እንነሳለን ብለዋል።

ለህዝብና ለሃገር ክብር የተሰው ጀግኖቻችን ዘላለማዊ ክብር ይገባቸዋልም ነው ያሉት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.